ማኪ ሳል ወደ ተመድ አመራርነት ጉዞ ያለ አፍሪካ የተቀናጀ ድጋፍ አጠራጣሪ መሆኑን ተንታኙ ገለፁ
19:49 16.02.2026 (የተሻሻለ: 19:54 16.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ማኪ ሳል ወደ ተመድ አመራርነት ጉዞ ያለ አፍሪካ የተቀናጀ ድጋፍ አጠራጣሪ መሆኑን ተንታኙ ገለፁ
የአፍሪካን እጩ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊነት ቦታ ማቅረብ ለአኅጉሪቱ እጅግ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው የግራዴክ ለትርፍ ያልተቋቋ ድርጅት ባልደረባ ጅብሪል ኒንግ ገልጸዋል።
ኒንግ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በጎርጎሮሳዊያኑ 2026 መጨረሻ ክፍት በሚሆነው የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊነት ቦታ ላይ የቀድሞው የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ሊወዳደሩ ስለሚችሉበት ሁኔታ ተንትነዋል።
ማኪ ሳል ለቦታው የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው በተዘዋዋሪ የጠቆሙ ሲሆን፣ ይህ ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማው ባለፈው መስከረም ነበር። በጥር ወር መጨረሻ የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማይ ፋዬ በኮንጎ ባደረጉት ጉብኝት ወቅትም ጉዳዩ ዳግም ተነስቷል። በወቅቱ የኮንጎ ባለሥልጣናት የማኪ ሳል እጩነት "የሁሉም የአፍሪካ ሀገራትን ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል" የሚል ተስፋ ሰጥተው ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X