አውሮፓውያን ልውጥ ዘረ መልን እና የተከለከሉ ኬሚካሎችን አፍሪካ ውስጥ የሚያስፋፉት የበሽታ እና የመድኃኒት ትስስር ለመፍጠር ነው – የአፍሪካ የፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል

አውሮፓውያን ልውጥ ዘረ መልን እና የተከለከሉ ኬሚካሎችን አፍሪካ ውስጥ የሚያስፋፉት የበሽታ እና የመድኃኒት ትስስር ለመፍጠር ነው – የአፍሪካ የፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሴጉን አዲባዮ፣ በአፍሪካ ውስጥ ለውጥ ዘረመሎችን በማስፋፋት፣ በግብርና ግብዓትነት ስም ጊዜ ያለፈባቸውን ከሚካሎች በማሰራጭት እና በራሳቸው አገር ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የታገዱ የአረም መድኃኒቶችን በማከፋፈል የተጠመዱት ውስብስብ የጤና ችግሮችን ሆን ብሎ ለመፍጠር መሆኑን ከአፍሪካ ሕብረት ማጠቃለያ ጎን ለጎን ለሚዲያዎች መግለጫ ወቅት ለስፑትኒክ አፍሪካ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ጠቁምዋል፡፡
“ዘሩን ሲሸጡላችሁ አብሮት ጥቅም ላይ መዋል ያለበትን ኬሚካል አይነግሯችሁም። መጀመሪያ 10 ሊትር ኬሚካል ትጠቀማላችሁ፤ ቀጥሎ ግን አረሞች ስለሚለማመዱ 20 ሊትርና ከዚያ በላይ እንድትጠቀሙ ትገደዳላችሁ። ይህ ሁለተኛው ችግር ነው። ሦስተኛው ደግሞ ዘሩ በኬሚካል መካከል እንዲበቅል ተደርጎ በላብራቶሪ የተቀነባበረ በመሆኑ፣ ተክሉ ኬሚካሉን ወደ ውስጡ ይመጥጣል። እናንተም ያንን ተክል ስትበሉ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የሰውነት ክፍሎቻችሁ መታመም ይጀምራሉ።” ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ዘሩንና ኬሚካሉን የሸጡ ሰዎች፣ ሕመም ሲመጣ ራሳቸው መድኃኒቱን የሚነግዱ መሆናቸውን ዶክተር ሴጉን አዲባዮ ተናግረዋል፡፡
“ለምሳሌ ‘ባየር’ የተባለውን ኩባንያ መመርመር ትችላላችሁ፤ መድኃኒቱንም፣ ዘሩንም፣ ኬሚካሉንም የሚያመርቱት እነሱ ናቸው። ስለነዚህ ፖሊሲዎች መጥፎ ጎን ማንም አይነግራችሁም።” ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በስጋትነት ያነሷቸው ተጨማሪ ቁልፍ ነጥቦች፦
እነዚህ ዘሮች አሁን በማላዊ፣ በናይጄሪያና በጋና ገብተዋል። ታንዛኒያ ሞክራው ጉዳቱን ስላየች አግዳዋለች።
እነዚህን ነገሮች የሚገፉት ሰዎች ብዙ ገንዘብ ስላላቸው ለፖለቲከኞች በመስጠት እንዲጸድቅ ያደርጋሉ።
ከጊዜ በኋላ ግን የተፈጥሮ ዘሮቻችሁን ታጣላችሁ። ከዚያም በነዚያ ሰዎች ላይ ጥገኛ ትሆናላችሁ።
በስተመጨረሻም "የምንፈልገውን ፖሊሲ (“ኤል ጂ ቢ ቲ") ካልተቀበላችሁ ዘር አንሸጥላችሁም" ሊሏችሁ ይችላሉ።
ዶክተር ሴጉን አዲባዮ፣ “ለዚህ ነው በሩሲያ ውስጥ ጂ ኤም ኦ መትከል እንደ ሽብርተኝነት የሚቆጠረው። ይህ የባዮሎጂ ጥቃት ነው። በገዛ እጃችሁ ድርቅንና ረሃብን መጋበዝ ነው።” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ወደ አፍሪካ የሚመጡ አብዛኞቹ ፖሊሲዎች አዲስ አለመሆናቸውን በመጥቀስ ምክረ ሐሳባቸውን ለግሰዋል፦
🟠 የእኛ ሥራ የፖሊሲዎቹን ዓላማ ማወቅ ነው።
🟠 አንዳንዶቹ ለአጭር ጊዜ ጠቃሚ ቢመስሉም ለረጅም ጊዜ ግን አውዳሚ ናቸው።
🟠 ብዙ የአፍሪካ መንግሥታት ግን የአጭር ጊዜ ጥቅሙን እንጂ የረጅም ጊዜ ጉዳቱን አያስተውሉም።
🟠 አፍሪካ ለብዙ ዓመታት ባለችበት የቆመችው ወይም ወደ ኋላ የምትመለሰው ለዚህ ነው ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X