የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራግቺ ከአሜሪካ ጋር ከሚደረገው ድርድር አስቀድሞ በጄኔቫ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ሃላፊ ጋር ተገናኙ
17:08 16.02.2026 (የተሻሻለ: 17:24 16.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራግቺ ከአሜሪካ ጋር ከሚደረገው ድርድር አስቀድሞ በጄኔቫ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ሃላፊ ጋር ተገናኙ
“ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ እውነተኛ ሃሳቦችን ይዤ ጄኔቫ እገኛለሁ። በድርድር ጠረጴዛው ላይ በፍጹም የማይቀርበው ነገር ቢኖር፣ ለዛቻ ተንበርክኮ እጅ መስጠት ነው” ሲሉ አባስ አራግቺ ተናግረዋል።
እሁድ ዕለት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከኢራን ጋር የሚደረግ ማንኛውም ስምምነት “ለእስራኤል ደህንነት ብቻ ሳይሆን ለአሜሪካ፣ ለቀጣናው እና ለዓለም ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ” አራት ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት አለበት ሲሉ ተከራክረዋል። (ቪዲዮ 2)
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፃ ቅድመ ሁኔታዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦
▪ ኢራን ያከማቸችው የበለፀገ ዩራኒየም በሙሉ እንዲወገድ፤
▪ የኢራን የዩራኒየም የማበልጸግ አቅም እስከመጨረሻው እንዲፈርስ፤
▪ በእስራኤል ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከል የባሊስቲክ ሚሳኤል የተኩስ ርቀት ከ300 ኪ.ሜ እንዳያልፍ ገደብ እንዲቀመጥ፤
▪ ቀጣናዊ የውክልና መረቦችን ጨምሮ የኢራን “የሽብር ዘንግ” ሙሉ በሙሉ እንዲፈርስ።
▫ ኢራን በበኩሏ ሰላማዊ በሆነው የኒውክሌር መርሃ ግብሯ አካል ዩራኒየም የማበልጸግ መብቷ ሊከበርላት እንደሚገባ ደጋግማ ትገልጻለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/