አፍሪካ የክትባት ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ "አቺቭ አፍሪካ" የተሰኘውን ንቅናቄ ይፋ አደረገች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ የክትባት ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ "አቺቭ አፍሪካ" የተሰኘውን ንቅናቄ ይፋ አደረገች
አፍሪካ የክትባት ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ አቺቭ አፍሪካ የተሰኘውን ንቅናቄ ይፋ አደረገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.02.2026
ሰብስክራይብ

አፍሪካ የክትባት ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ "አቺቭ አፍሪካ" የተሰኘውን ንቅናቄ ይፋ አደረገች  

የኢኒሼቲቩ (ACHIEVE Africa) ዋና ግብ አፍሪካ የክትባት ማሸጊያ ማዕከል ብቻ ሳትሆን የክትባት ግኝትና ምርምር መነሻም እንድትሆን ማስቻል እና ከክትባት ግኝትና ከክሊኒካዊ ሙከራ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ስርጭት ያለውን አጠቃላይ የእሴት ሰንሰለት በአኅጉሪቱ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ተገልጿል።  

የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣  ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት እ.ኤ.አ በ2040 የክትባት ፍላጎትን 60 በመቶ በአኅጉር ውስጥ ለማሟላት ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ግንባር ቀደም ሚና እየተወጣች መሆኑን ገልፀዋል።

በመድኃኒት ዘርፍ፣ የአገር ውስጥ ፍላጎትን ሽፋን ከ8 በመቶ ወደ 42 በመቶ ማደጉንና ወደ 60 በመቶ የማሳደግ እቅድ መኖሩንም ጠቁመዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0