የሙኒክ የደህንነት ጉባኤ የአውሮፓን መሰነጣጠቅ መግለጡ ተዘገበ

ሰብስክራይብ

የሙኒክ የደህንነት ጉባኤ የአውሮፓን መሰነጣጠቅ መግለጡ ተዘገበ

​የፈረንሳይ እና የጀርመን ግንኙነት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ መውደቁንና አኅጉሪቱ የመበታተን አደጋ እንደተጋረጠባት በሙኒክ የደህንነት ጉባኤ ላይ የተቀረጸ ቪዲዮ በዋቢነት የተጠሰ ሲሆን፤ ቪዲዮው የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን የጀርመኑን መራኄ መንግሥት ፍሬድሪች ሜርዝን ሰላም ለማለት ሲሞክሩ፣ ሜርዝ ግን ከስታርመር ጋር እያወሩ ማክሮንን ችላ ሲሏቸው ያሳያል ሲል አንድ የጀርመን ጋዜጣ ዘግቧል።

አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ ዲፕሎማት ለጋዜጣው ሲናገሩ፣ "ጀርመኖች ከፈረንሳይ ጋር ያላቸው ትልቁ ችግር ፈረንሳውያንን ከአሁን በኋላ አለማመናቸው ነው" ብለዋል። በርሊን  ፓሪስን "ንግግሯ ብዙ፣ ተግባሯ ግን ጥቂት" በማለት ትተቻለች።

​ከየካቲት 3 እስከ 8 በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ አውሮፓ ግራ የተጋባች፣ ፈረንሳይ የደከመች፣ ጀርመንም ግልጽ ስትራቴጂ የሌላት መስለው መታየታቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።

​በተጨማሪም ፣ አውሮፓውያን ከዩክሬን የሰላም ንግግሮች መገለላቸው እና በሀገራቸውም የህዝብ ድጋፍ እየቀነሰባቸው በመምጣቱ ብቸኝነት እየተሰማቸው መሆኑን ዘገባው አጽንኦት ሰጥቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0