ኢትዮጵያ የቡና መማማሪያ ማዕከል ሥራ አስጀመረች
15:26 16.02.2026 (የተሻሻለ: 15:34 16.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የቡና መማማሪያ ማዕከል ሥራ አስጀመረች
ማዕከሉ በይዘት ደረጃ ቡና ከዘር እስከ ወጪ ንግድ ድረስ ምን እንደሚመስል እውቀትና ክህሎት ማስጨበጫ ማዕከል እንደሚሆን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
የማዕከሉ ትኩረቶች፦
የኢትዮጵያ ቡና ታሪክ፣
የሴቶች ሚና በቡናው ዘርፍ፣
ቡና ለኢኮኖሚና ማኅበራዊ ሕይወት ያሉት ጠቀሜታዎችን እና
ሌሎች የባሕልና የትምህርት ርዕሰ ጉዳዮች
ዓለም አቀፍ ርዕይ፦ የቡና ሁለንተናዊ ጉዳይ ለዓለም የሚተዋወቅበት ማዕከል የመሆን ግብም ተቀምጦለታል።
በትናትናው ዕለት ተመረቆ የተከፈተው የማዕከሉ እንቅስቃሴ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን ቀጣዩ ምዕራፍ ዲጂታላይዝ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሁለቱንም ማዕከሉን የማደራጀት ምዕራፎች እየሰራ የሚገኘው በአገር በቀል ድርጅት እንደሆነ ባለሥልጣኑ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X