የዩክሬን የቀድሞ የኢነርጂ ሚኒስትር በሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዩክሬን የቀድሞ የኢነርጂ ሚኒስትር በሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ
የዩክሬን የቀድሞ የኢነርጂ ሚኒስትር በሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.02.2026
ሰብስክራይብ

የዩክሬን የቀድሞ የኢነርጂ ሚኒስትር በሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ

​የዩክሬን ብሔራዊ የፀረ-ሙስና ቢሮ (ናቡ) የቀድሞውን የኢነርጂ ሚኒስትር ጀርመን ጋሉሽቼንኮን፣ በሀገሪቱ የኢነርጂ ዘርፍ ውስጥ ከታየው የሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

​ "ዛሬ፣ የቀድሞው የኢነርጂ ሚኒስትር የሃገሪቱን ድንበር ለማቋረጥ ሲሞክሩ በ'ሚዳስ' የሙስና መዝገብ ማዕቀፍ ውስጥ በናቡ መርማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በሕግ መስፈርቶች እና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት የመጀመሪያ ደረጃ የምርመራ እርምጃዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ" ሲል ናቡ በቴሌግራም ገጹ አስታውቋል።

ባለፈው ህዳር ናቡ በኢነርጂ ዘርፉ ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን፣ በዘመቻው ወቅት የተገኙ በውጭ ምንዛሬ የተሞሉ ቦርሳዎችን የሚያሳዩ ምስሎችንም ይፋ አድርጎ ነበር።

​ናቡ በጋሉሽቼንኮ መኖሪያ ቤት፣ እንዲሁም በመንግስት የኒውክሌር ኢነርጂ ኤጀንሲ ውስጥ ፍተሻዎችን አካሂዷል።

​ኤጀንሲው በወቅቱ ዩክሬንን ጥሎ የሸሸውን የዘለንስኪ የቅርብ ረዳት ቲሙር ሚንዲች መኖሪያ ቤትም ፈትሿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0