የጋናው የሶፍትዌር ኩባንያ ሽሪንኪው ሊሚቲድ በብሩህ ፋይናንስ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ገባ
18:15 15.02.2026 (የተሻሻለ: 18:24 15.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የጋናው የሶፍትዌር ኩባንያ ሽሪንኪው ሊሚቲድ በብሩህ ፋይናንስ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ገባ
የተቋማቱ ትብብር ከአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣሙ ዘመናዊ የዲጂታል መፍትሄዎችን በማስተዋወቅ፣ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማፋጠን ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ብሩህ ፋይናንስ፣ ሽሪንኪው የሚያለማቸውን የዲጂታል ኢንሹራንስ፣ የባንክ አገልግሎት ሲስተሞች፣ የአስተዳደር እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ ሥርዓት የቴክኖሎጂ ምርቶች የኢትዮጵያ ብቸኛ ወኪል ሆኖ ያገለግላል።
ትብብሩ በአፍሪካ በማደግ ላይ ባሉ ገበያዎች መካከል የሚደረግ የደቡብ-ደቡብ የቴክኖሎጂ ትብብር ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል ሲሉ የግል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X