ስፑትኒክ 'የተለያዩ እይታዎችን እና የመረጃ ትርጓሜዎችን’ ወደ አፍሪካ ያመጣል - የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
18:01 15.02.2026 (የተሻሻለ: 18:04 15.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ስፑትኒክ 'የተለያዩ እይታዎችን እና የመረጃ ትርጓሜዎችን’ ወደ አፍሪካ ያመጣል - የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አፍሪካ የተወሰኑ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት፣ “ መረጃን ለራስ ጥቅም ብለው የሚያዛቡ አካላት መሣሪያዎች” መሆናቸውን የተረዳች ሲሆን፣ እንደ ስፑትኒክ ያሉ ኤጀንሲዎች ደግሞ ብዝሃነትን መሠረት ያደረገ አመለካከት ያንፀባርቃሉ" ሲሉ ካራሞኮ ዣን ማሪ ትራኦሬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም “ሰዎች መረጃዎችን የማገናዘብ እና የማነፃፀር ዕድል ስላላቸው፣ የዚህ ተቋም ዝና እየናኘ መምጣቱ አያስደንቀኝም። በእርግጥ ገና ብዙ የሚቀሩ ስራዎች አሉ፤ ምክንያቱም ወደ ሚዲያው ዓለም ሲገባ ሆነ ብለው ፍጹም የሐሰት መረጃዎችን የሚፈጥሩ ብዙ አካላት አሉ” ብለዋል።
እነዚህ የሐሰት መረጃ ዘመቻዎች ዓላማቸው፣ “በሳህል አገራት ጥምረት ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ወደ እውነተኛ ውህደት የሚያመራውን ጉዞ” ለማዘግየት ነው ብለዋል ትራኦሬ።
የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን አፍሪካ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ሊያሰፉ ይችላሉ፤ ይህ ዕድል በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና በቡርኪና ፋሶ አቻቸው መካከል በቅርቡ በተደረገው ውይይት ተነስቷል።
የቡርኪና ፋሶው ሚኒስትር፣ “የተወሰኑ የመገናኛ ብዙኃን” በአፍሪካ እና በአውሮፓ ሕዝቦች መካከል የተሳሳቱ እውነታዎችን ማሰራጨታቸውን በሚቀጥሉበት በዚህ ወቅት፣ እንዲህ ያለው ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
“የሚዲያ ትብብርን ማጠናከር አስፈላጊ ነው። ነገር ግን የራሳችን መገናኛ ብዙኃንም ስራቸውን እንዲወጡ ማለትም፣ ግንዛቤን የማስጨበጥ፣ መረጃ የመስጠት፣ የፍትህ፣ የማስተካከያ እና የሚዲያውን ዐውድ የማፅዳት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ ተጨማሪ ግብዓቶችን መስጠት ያስፈልጋል” ሲሉ ሚኒስትሩ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X