'በባሪያ ንግድ ዘመን የተፈጸሙ በደሎች ተጽእኖዎች እንደቀጠሉ ናቸው' - የጋና ፕሬዝዳንት ዶራማኒ ማሃማ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ'በባሪያ ንግድ ዘመን የተፈጸሙ በደሎች ተጽእኖዎች እንደቀጠሉ ናቸው' - የጋና ፕሬዝዳንት ዶራማኒ ማሃማ
'በባሪያ ንግድ ዘመን የተፈጸሙ በደሎች ተጽእኖዎች እንደቀጠሉ ናቸው' - የጋና ፕሬዝዳንት ዶራማኒ ማሃማ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.02.2026
ሰብስክራይብ

'በባሪያ ንግድ ዘመን የተፈጸሙ በደሎች ተጽእኖዎች እንደቀጠሉ ናቸው' - የጋና ፕሬዝዳንት ዶራማኒ ማሃማ

የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ አገራቸው በመጪው መጋቢት ላይ በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ላይ ለማቅረብ ባዘጋጀችው እና የባርያ ንድ ሰለባ ለሆኑ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትሕ መጠየቅን ዓላማው ባደረገው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

“ዓላማችን ግልጽ ነው፤ እሱም የባርያ ንግድ ዘመን ሕገወጥ ዝውውር እና በደል ለተፈጸመባቸው አፍሪካውያን ፍትሕን በማስገኘት ዙሪያ መግባባትን መፍጠር ነው።” ብለዋል።

ይህ የውሳኔ ሃሳብ በማንኛውም ሀገር ላይ ያነጣጠረ አይደለም ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ይልቁንም ወደ እውነት፣ እውቅና እና እርቅ የሚያመራ መሆኑን ተናግረዋል። "ታሪክን ሊያጠፉት ባይቻልም እውቅና ሊሰጠው ግን ይገባል።” ሲሉም አሳስበዋል፡፡

"በአፍሪካውያን ላይ በባሪያ ንግድ ዘመን ሕገ ወጥ ዝውውር እና ዘረኝነትን መሠረት ያደረገ በደል ተፈጽሞባቸዋል። እነዚህ በደሎች ዘመናዊውን ዓለም የቀረጹ መሠረታዊ ወንጀሎች ናቸው። ውጤታቸውም መዋቅራዊ በሆነ አድልዎ እና በኢኮኖሚያዊ አቅም መዳከም በመሳሰሉ አሉታዊ ውጤቶች መገለጡን ቀጥሏል።” 

ድራማኒ ማሃማ የውሳኔ ሃሳቡ ስለ መከፋፈል ላይ ሳይሆን ስነ-ምግባር ላይ ያተኮረ መሆኑን አስታውሰው፣ በመቀጠልም ወደ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ፣ ወደ አፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን፣ ወደ ቀይ መስቀል እና ተያያዥ አካላት እንዲሁም ወደ አባል ሀገራት ማድረሱን እንደሚቀጠሉ ማስታወቃቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0