የአፍሪካ ሕብረት 'የባሪያ ንግድ' በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ነው ሲል አወጀ
17:33 15.02.2026 (የተሻሻለ: 18:04 15.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሕብረት 'የባሪያ ንግድ' በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ነው ሲል አወጀ
ሕብረቱ ዛሬ ፍጻሜውን ባገኘው 39ኛ የመሪዎች ጉባኤው በአፍሪካ እና በአፍሪካውያን ላይ የተፈጸመውን የባሪያ ንግድ በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል አድርጎ እውቅና እንዲሰጥ በቀረበለት ሐሳብ ላይ ተወያይቷል።
በውይይቱ የባሪያ ንግዱን በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል አድርጎ ስለማወጁም ነው የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ የሱፍ የተናገሩት።
የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ የትራንስ አትላንቲክ የባሪያ ንግድን እና ባርነትን በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል አድርጎ የመፈረጅ ሐሳብ እንዳለው መገለጹን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
ከዚያ በፊት ጉዳዩን በተመለከተ አኅጉራዊ መግባባት፣ አንድነትና ትብብር እንዲደረግ ጋና ከሰሞኑ ከጉባኤው ቀደም ብሎ ሲካሄድ በነበረው የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ መጠየቋ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X