አፍሪካ ከምስራቁ የኢኮኖሚ ክፍል ጋር ያላት አጋርነት ኢንተርፕራይዞችን ማሳደግ ላይ ሊያተኩር ይገባል - የምጣኔ ሐብት ባለሙያ

ሰብስክራይብ

አፍሪካ ከምስራቁ የኢኮኖሚ ክፍል ጋር ያላት አጋርነት ኢንተርፕራይዞችን ማሳደግ ላይ ሊያተኩር ይገባል - የምጣኔ ሐብት ባለሙያ

አኅጉሪቱ ከቻይና፣ ደቡብ ምስራቅ እስያ እና ህንድ ጋር ያላት ትብብር፣ የአፍሪካ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ወደ ጠንካራ የእሴት ሰንሰለት እንዲገቡ በር የሚከፍት መሆን እንዳለበት የፓን አፍሪካ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ገና ገልጸዋል።

የምጣኔ ሐብት ባለሙያው  "የምንፈልገው ግንኙነት የተፈጥሮ ሐብትን አውጥቶ ከመሸጥ የተሻገረ ነው፡፡ እንደ አኀጉር ከእሴት ሰንሰለት ጋር በተያያዘ ከእነዚህ እምቅ አጋሮች ምን እንደምትፈልግ በግልጽ የምናስረዳበት ጊዜ ነው።" ሲሉ ተናግረዋል።

ክቡር ገና ከአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ የተካሄደውን የመጀመሪያው የአፍሪካ የንግድ መሪዎች ቡድን መድረክ ተክትሎ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተጨማሪ ሐሳቦችንም አንስተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0