የአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ሕብረት እና የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና የአፍሪካን የምግብ ሉዓላዊነት ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
18:41 14.02.2026 (የተሻሻለ: 18:44 14.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ሕብረት እና የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና የአፍሪካን የምግብ ሉዓላዊነት ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
የተፈረመው ስምምነት የግብርና ምርቶችን እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ እንዲሁም፣ ለሦስት ዓመታት ያህል የአፍሪካን የምግብ ገቢ ወጪ ለመቀነስ የቴክኒክ ክህሎቶችን እና የፖሊሲ እውቀቶችን ያቀናጃል።
ተነሳሽነቱ ለአነስተኛ ገበሬዎችና መደበኛ ላልሆኑ ነጋዴዎች የገበያ ተደራሽነትን የሚገድቡ ግብር ነክ ያልሆኑ መሰናክሎችን በማስወገድ የምግብ ዋስትና እጥረትን ለመፍታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ሕብረት ፕሬዝዳንት አሊስ ሩህዌዛ እንደገለጹት፣ የሁለቱ ተቋማት አጋርነት፦
የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን በመገንባት እና የምግብ ስርዓቶችን ከአካባቢያዊ ተግዳሮቶች በመጠበቅ ላይ ትኩረት ያደርጋል።
የምግብ መተላለፊያ መስመሮችን እና ምርታማ አካባቢዎችን ከግብርና ማቀነባበሪያ ዞኖች ጋር በማገናኘት በአፍሪካ ያለውን የግብርና ልማት እና የምግብ ዋስትና የበለጠ ለማሳደግ አልሟል ስትል በፊርማው ሥነ -ስርዓት ላይ የተገኘችው የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግባለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X