ሩሲያ እና ቡርኪና ፋሶ የሳይንስ እና የትምህርት ትብብራቸውን ለማሳደግ ሁለት ስምምነቶችን ተፈራረሙ
17:14 14.02.2026 (የተሻሻለ: 17:24 14.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ቡርኪና ፋሶ የሳይንስ እና የትምህርት ትብብራቸውን ለማሳደግ ሁለት ስምምነቶችን ተፈራረሙ
በሞስኮ በተካሄደ ስብሰባ የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሩሲያ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የሚከተሉትን ስምምነቶች ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቶቹም፡-
በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት፤
በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ሥራዎች ዘርፍ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት።
የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካራሞኮ ዣን ማሪ ትራውሬ እንደገለጹት፣ እነዚህ ሰነዶች በፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራውሬ ምክረ ሐሳብ መሠረት ሃገሪቱ አሁን ካለችበት አጠቃላይ የትምህርት ሥርዓት ወጥታ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትኩረት ወደሚሰጥ ተግባራዊ አሠራር እንድትሸጋገር ይረዳታል።
የሩሲያው ሚኒስትር ቫለሪ ፋልኮቭ በበኩላቸው፣ ይህ ስምምነት ላለፉት ሁለት ዓመታት የተደረገ የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን ገልጸው፣ የአካዳሚክ ልውውጥን እና ሳይንሳዊ ምርምርን ለማሳደግ መሠረት የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia