ኢትዮጵያ የጉዞ ጥራትና ደህንነት ለማሻሻል ከሰበታ እስከ ናጋድ ጅቡቲ ያለውን የባቡር መስመር ጥገና እያደረገች መሆኑን አስታወቀች
15:22 14.02.2026 (የተሻሻለ: 15:34 14.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የጉዞ ጥራትና ደህንነት ለማሻሻል ከሰበታ እስከ ናጋድ ጅቡቲ ያለውን የባቡር መስመር ጥገና እያደረገች መሆኑን አስታወቀች
ይህም የባቡር መስመሩን ጥራት እና የደህንነት መመዘኛዎችን በተሻለ ደረጃ ለማስቀመጥ ከማገዙም በላይ የባቡር ምልልስና ፍጥነትን ለማሳደገግ እንደሚያግዝ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ ገልጸዋል፡፡
የጥገና ፕሮጀክቱ፦
🟠 የጭነት ባቡሮችን የጉዞ ፍጥነት በሰዓት 60 ኪ.ሜ ከነበረበት ወደ 67 ኪ.ሜ በሰዓት እንዲጓዙ ያስችላል፡፡
🟠 የመንገደኞች ባቡር የጉዞ ፍጥነት በሰዓት 70 ኪ.ሜ ከነበረበት ወደ 90 ኪ.ሜ በሰዓት እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
🟠 ለስምንት ዓመታት ያለ አገልግሎት ተዘግተው የነበሩ መስመሮችን ወደ አገልግሎት ያስገባል፡፡
🟠 የባቡር መስመሩ አሮጌ ቁሳቁሶች እንዲወገዱና በአዳዲስ ግብአቶች እንዲተኩ ያደርጋል፡፡
በመካሄድ ላይ የሚገኘው የጥገና ሥራ የአራት ወራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው በማኅበራዊ የፅር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia

1/3
© telegram sputnik_ethiopia

2/3
© telegram sputnik_ethiopia

3/3
© telegram sputnik_ethiopia
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
3/3
© telegram sputnik_ethiopia