የናይሮቢ ስታርትአፕ ከአኅጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና ጋር የተገናኙ ዲጂታል የንግድ ማዕከሎችን ይፋ አደረገ፤ የኢትዮጵያ ባንኮችንም እያማከረ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይሮቢ ስታርትአፕ ከአኅጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና ጋር የተገናኙ ዲጂታል የንግድ ማዕከሎችን ይፋ አደረገ፤ የኢትዮጵያ ባንኮችንም እያማከረ ነው
የናይሮቢ ስታርትአፕ ከአኅጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና ጋር የተገናኙ ዲጂታል የንግድ ማዕከሎችን ይፋ አደረገ፤ የኢትዮጵያ ባንኮችንም እያማከረ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.02.2026
ሰብስክራይብ

የናይሮቢ ስታርትአፕ ከአኅጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና ጋር የተገናኙ ዲጂታል የንግድ ማዕከሎችን ይፋ አደረገ፤ የኢትዮጵያ ባንኮችንም እያማከረ ነው

ሪል ሶርስስ አፍሪካ የተሰኘው ስታርትአፕ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የገነባቸውን ሁለት ዲጂታል መድረኮችን በትናትናው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደ ሥነ -ስርዓት አስጀምሯል።

"ቢያሻራ ሊንክ"፡- የመጀመሪያው ሲሆን፣ ኤምባሲዎች፣ ላኪዎች እና ባለሀብቶች የአፍሪካ አሕጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር የተጣጣሙ የንግድ ዕድሎችን እንዲመዘግቡ እና እንዲከታተሉ ያስችላቸዋል።

"ዲል ሃውስ"፡- በማለት የሰየመው መድረክ፣ ስምምነቶችን የሚረጋገጥ ፣ ከፋይናንስ ጋር በማገናኘት እስከ ውል ማጠናቀቂያ ድረስ በማድረስ እንደ አስፈጻሚ አካል የሚሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ሪል ሶርስስ አፍሪካ በአሁኑ ወቅት ከቡና ባንክ እና ከአዋሽ ባንክ ጋር የንግድ ፋይናንስን፣ የሐዋላ ልውውጥን እና የሀገር ውስጥ ላኪዎችን ግብይት ለማቀላጠፍ ንግግር እያደረገ ይገኛል ሲሉ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገበዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0