የኢትዮጵያ የስርዓተ-ምግብ ማሻሻያ እርምጃዎች ተምሳሌታዊ ውጤት አፍርተዋል - የሌሴቶ ንጉሥ ሌቲ ሳልሳዊ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የስርዓተ-ምግብ ማሻሻያ እርምጃዎች ተምሳሌታዊ ውጤት አፍርተዋል - የሌሴቶ ንጉሥ ሌቲ ሳልሳዊ
የኢትዮጵያ የስርዓተ-ምግብ ማሻሻያ እርምጃዎች ተምሳሌታዊ ውጤት አፍርተዋል - የሌሴቶ ንጉሥ ሌቲ ሳልሳዊ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.02.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የስርዓተ-ምግብ ማሻሻያ እርምጃዎች ተምሳሌታዊ ውጤት አፍርተዋል - የሌሴቶ ንጉሥ ሌቲ ሳልሳዊ

ንጉሡ፣ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የህፃናት እንክብካቤ እና የስርዓተ-ምግብ ክፍልን ጎብኝተዋል፤ በጉብኝታቸው ኢትዮጵያ የእናቶችን እና የህፃናትን ጤና ለማሻሻል ያላትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

ግርማዊ ንጉሥ ሌቲ፣  “ውጤታማ የስርዓተ-ምግብ እርምጃ ህይወትን ያድናሉ” ሲሉ  አፅንኦት የሰጡ ሲሆን  ስርዓተ-ምግብ በሽታን በመከላከል እና የህፃናትን ሞት በመቀነስ ረገድ ያለውን ወሳኝ ሚናም ገልጸዋል።

 

በጉብኝቱ ወቅት  ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፣ "ስርዓተ-ምግብ  እና የህፃናትን ህልውና ማሳደግ የኢትዮጵያ የሰው ልጅ ካፒታል መሰረት መገንባት መሆኑን በመግለጽ ሀገሪቱ የምትከተለው የተቀናጀ አሰራር አስረድተዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0