ኒጀር ከፈረንሳይ ጋር ጦርነት ውስጥ ትገባለች - የሀገሪቱ ጄኔራል
20:18 12.02.2026 (የተሻሻለ: 20:24 12.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኒጀር ከፈረንሳይ ጋር ጦርነት ውስጥ ትገባለች - የሀገሪቱ ጄኔራል
በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በኒያሜ ስታዲየም በተሰበሰቡበት ይህን የተናገሩት ጄነራል ኢብሮ አማዶ፤ ፓሪስ ኒጀርን ማተራመስ ትሻለች ሲሉ በድጋሚ ከሰዋል።
ቀደም ሲል የፀደቀው የመንግሥት የክተት አዋጅ ሀገሪቱን ከፈረንሳይ ጋር ለሚደረገው ጦርነት ለማዘጋጀት የታሰበ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
ይህ መግለጫ ጥር 21 ምሽት በኒያሜ አየር ማረፊያ ላይ የደረሰውን ጥቃት የተከትለ ነው። በወቅቱ የኒጀር ፕሬዚዳንት ፈረንሳይ፣ ቤኒን እና ኮትዲቯር ጥቃት ፈፃሚዎቹን በገንዘብ ድጋፋዋል በማለት አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል።
የፈረንሳይ ጦር ጠቅላይ ኢታማዦር በበኩላቸው ክሱን ውድቅ አድርገዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X