ፕሬዚዳንት ሩቶ ከኢትዮጵያ ጋር አጋርነት በመፍጠር ለማንዴራ ከተማ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ቃል ገቡ

ሰብስክራይብ

ፕሬዚዳንት ሩቶ ከኢትዮጵያ ጋር አጋርነት በመፍጠር ለማንዴራ ከተማ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ቃል ገቡ

በሰሜን ኬንያ የሚታየውን ከፍተኛ የኃይል እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥታቸው ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለቀጣናው የኃይል ትስስር ትልቅ ተስፋ ነው የተባለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሲመረቅ ተገኝተው የነበሩት ፕሬዚዳንት ሩቶ፤ "በግዛቱ ያለውን አጣዳፊ የኃይል እጥረት ለመፍታት በአጭር ጊዜ ውስጥ የ3 ሜጋ ዋት ጄኔሬተር እንተክላለን፤ በተጓዳኝም ለዘላቂ መፍትሔ ማንዴራን ከኢትዮጵያ የኃይል መስመር ጋር የማገናኘት ሥራ እናፋጥናለን" ሲሉ ዛሬ በማንዴራ ስታዲየም በተካሄደ ፕሮግራም ላይ ተናግረዋል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ኬንያ ከግድቡ የሚገኘውን ትርፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመጠቀም የሚያስችል የኃይል ግዢ ስምምነት ለመፈራረም ዝግጁ ነች ብለው ነበር፡፡

“ኢንዱስትሪዎቻችንን፣ የቴክኖሎጂ ማዕከላቶቻችንን ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም ተወዳዳሪነትን አጠናክሮ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከኢትዮጵያ ጋር የኃይል ግዢ ስምምነት ለመፈራረም ዝግጁ ነን፡፡"

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0