አንጎላ በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከየካቲት 11 ጀምሮ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሐሳብ አቀረበች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአንጎላ በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከየካቲት 11 ጀምሮ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሐሳብ አቀረበች
አንጎላ በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከየካቲት 11 ጀምሮ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሐሳብ አቀረበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.02.2026
ሰብስክራይብ

አንጎላ በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከየካቲት 11 ጀምሮ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሐሳብ አቀረበች

የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራሲያው ሪፐብሊክ ያለውን ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለመ "የበይነ ኮንጎ ውይይት" ለማዘጋጀት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የአንጎላ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

እ.ኤ.አ 2022 በሎሬንሶ ሰብሳቢነት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በሩዋንዳ መካከል ያለውን ግንኙነት ፈር ለማስያዝ የተጀመረው "የሉዋንዳ ሂደት"፤ ከናይሮቢ ሂደት በተጓዳኝ በምስራቅ ኮንጎ ቀውስ ዙሪያ የኮንጎ ወገኖች ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ሲሠራ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ሂደቶች በአፍሪካ ኅብረት፣ በአንጎላ፣ በቶጎ እና በናይጄሪያ አሸማጋይነት ዳግም እንዲጀመሩ እየተደረገ ነው።

የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለሥልጣናት ጎረቤት ሀገር ሩዋንዳ ለኤም 23 አማፂ ቡድን ቀጥተኛ ድጋፍ ታደርጋለች ሲሉ ቢከሱም፤ ሩዋንዳ ግን የቀረበባትን ክስ ደጋግማ አስተባብላለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0