ሩሲያ ናይጄሪያውያንን በዩክሬን ጦርነት እንዲሳተፉ መልምላለች የሚሉ ዘገባዎች ከእውነት የራቁና ከሞስኮ ጋር ግንኙነት የላቸውም ስትል ውድቅ አደረገች
15:35 12.02.2026 (የተሻሻለ: 15:44 12.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ናይጄሪያውያንን በዩክሬን ጦርነት እንዲሳተፉ መልምላለች የሚሉ ዘገባዎች ከእውነት የራቁና ከሞስኮ ጋር ግንኙነት የላቸውም ስትል ውድቅ አደረገች
በዩክሬን ግጭት ውስጥ የናይጄሪያ ዜጎችን የሚያሳትፍ ምንም ዓይነት በመንግሥት የተደገፈ ፕሮግራም እንደሌለ የገለፁት በናይጄሪያ የሩሲያ አምባሳደር አንድሬ ፖዲየሊሼቭ፤ እንዲህ ዓይነት ምልመላ ሕገ-ወጥ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ያልተፈቀደላቸው ግለሰቦች ናይጄሪያውያንን ለመመልመል የሚያደርጉት የተናጠል ጥረት ከሩሲያ መንግሥት ጋር ግንኙነት የለውም ብለዋል። ሀገሪቱ በጉዳዩ ዙሪያ የምታገኘው ተዓማኒ መረጃ እንዲመረመር ለሩሲያ የሕግ አስከባሪ አካላት እንደምታጋራ ጠቀመዋል።
የሩሲያ እና ናይጄሪያ ይፋዊ ወታደራዊ ትብብር በሥልጠና እና በመሣሪያ ልውውጦች ላይ አተኩሮ በጥብቅ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እንደሚመራ አምባሳደሩ አስረድተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X