ናይጄሪያ በእንግሊዝ ጦር የተዘረፉ 116 የነሐስ ቅርሶችን አስመለሰች

ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ በእንግሊዝ ጦር የተዘረፉ 116 የነሐስ ቅርሶችን አስመለሰች

እ.ኤ.አ በ1897 የተዘረፉት እነዚህ ቅርሶች የእንጨት ቅርጻ ቅርጾችን፣ የዝሆን ጥርስ ውጤቶችን እና ቀደም ሲል በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ሙዚየም ይገኙ የነበሩ የንጉሣዊ ቤተሰብ የራስ ምስሎችን ያካትታሉ። እነዚህ ውድ ቅርሶች የተወሰዱት በአሁኑ ደቡባዊ ናይጄሪያ ከሚገኘውና የቀድሞው የቤኒን ግዛት ዋና ከተማ ከነበረችው ቤኒን ሲቲ ነው።

ቅርሶቹን የማስረከቡ ሂደት የተከናወነው የናይጄሪያ የሙዚየሞችና ቅርሶች ብሔራዊ ኮሚሽን እ.ኤ.አ በ2022 ባቀረበው ይፋዊ ጥያቄ መሠረት ነው።

የኮሚሽኑ ዋና ዳይሬክተር ኦሉግቢሌ ሆሎዋይ፤ የቅርሶቹ መመለስ የናይጄሪያውያንን ኩራት እና ክብር መልሶ ለመገንባት ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

በቅኝ ግዛት ዘመን የተዘረፉ የአፍሪካ ጥበባት እና ቅርሶች እንዲመለሱ የሚደረገው ጥረት ሰፊና ብዙ ጊዜ የወሰድ እንቅስቃሴ አካል ነው። አሁንም በመቶዎች የሚቆጠሩ የምዕራባውያን ሙዚየሞች መሰል ቅርሶችን በእጃቸው ይዘው ይገኛሉ።

አፍሪካ እነዚህን ቅርሶች ለማስመለስ ለበርካታ አስርት ዓመታት ስትታገል የቆየች ቢሆንም ቅርሶቹን በያዙት ተቋማት በኩል የሚቀርቡ የሕግ ተግዳሮቶች ሂደቱን ሲያዘገዩት ቆይተዋል።

በቅርቡ የተመዘገቡ መሰል ክስተቶች፦

ግብፅ፦ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ 30 ሺ ቅርሶችን ያስመለሰች ቢሆንም አሁንም ከበርሊን የነፈርቲቲን ምሥል እንዲሁም ለንደን የሚገኘውን የሮዜታ ድንጋይ ለማስመለስ እየጣረች ትገኛለች።

ጋና፦ በቅርቡ ከ130 በላይ የአሻንቲ ንጉሣዊ ቤተሰብ ቅርሶችን ከአውሮፓ አስመልሳለች

ኢትዮጵያ፦ የጀግናው የራስ ደስታ ዳምጠው ጎራዴ እና አልባሳት በጣሊያን ለጨረታ መቅረባቸው ከባድ ድንጋጤ መፍጠሩ ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0