የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም ዙሪያ አዲስ ማሻሻያዎችን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም ዙሪያ አዲስ ማሻሻያዎችን ይፋ አደረገ
19 ዋና ዋና የመመሪያ ለውጦችን የያዘው የብሔራዊ ባንክ ማሻሻያ፤ ማንኛውም ነዋሪ ዜጋ ወደ ሀገር ይዞት የመጣውን የውጭ ምንዛሪ ያለ ጉምሩክ ሰነድ በባንኮች መመንዘር ወይም በሂሳቡ ማስቀመጥ እንደሚችል አስታውቋል።
ባንኮች ለደንበኞቻቸው ለውጭ ሀገር ክፍያና ለኤሌክትሮኒክ ግብይት የሚያገለግል ዓለም አቀፍ ካርድ እንዲያዘጋጁ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች በእጃቸው የሚይዙት ጥሬ ገንዘብ መጠን ከካፒታላቸው 10 በመቶ ከነበረበት ወደ 25 በመቶ ከፍ እንዲል የተደረገ ሲሆን ለቪዛና ፓስፖርት እድሳት ምንዛሪ መሸጥ እንዲችሉ ፍቃድ አግኝተዋል።
ሌሎች ቁልፍ ማሻሻያዎች፦
ኢትዮጵያውያን ዜጎች እስከ 3 ሺህ ዶላር በሕጋዊ መንገድ በውጭ ሀገር ለሚገኝ ቤተሰብ መላክ ይቻላሉ፣
የአገልግሎት ላኪዎች የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሪ 100 በመቶ በሂሳባቸው ውስጥ ያለ ምንም የጊዜ ገደብ እንዲይዙ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፣
ድርጅቶች የመዋዕለ ነዋያቸውን ሁኔታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እያስመረመሩ በሌላ ሀገር መዋዕለ ነዋያቸውን ፈሰስ ማድረግ እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡
ባንኮች ከካፒታላቸው ከ10 በመቶ ያልበለጠ ለግሉ ዘርፍ የውጭ ሀገር ብድር ዋስትና መስጠት ይችላሉ፣
የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስተሮች፣ ኤምባሲዎችና በሀገር ውስጥ የሚሠሩ ዓለምአቀፍ ተቋማት ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ በባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡
ሙሉ ማሻሻያውን ከላይ በተያያዘው ይፋዊ መግለጫ መመልከት ይችላሉ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
