ዚምባብዌ የእሴት ሰንሰለትን ለማሻሻል የባትሪ ማዕድናት ማቀነባበሪያን እያፋጠነች ነው - የማዕድን ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
18:36 11.02.2026 (የተሻሻለ: 18:44 11.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ የእሴት ሰንሰለትን ለማሻሻል የባትሪ ማዕድናት ማቀነባበሪያን እያፋጠነች ነው - የማዕድን ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
የሙታፓ ኢነርጂ ማዕድናት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢኖሰንት ሩክዌዛ፤ ኩባንያቸው እስከዚህኛው ዓመት ሰኔ ወር ድረስ በሳንዳዋና ሊቲየም ማዕድን ማውጫ ላይ የሊቲየም ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እንደሚጀምር ገልፀዋል።
“ለባትሪ ምርት የሚያገለግለውን ሰልፌት በተመለከተ የተወሰነ ጊዜ ያስፈልገናል፤ ነገር ግን በሥራው ላይ ነን። ምክንያቱም እ.ኤ.አ እስከ 2027 ድረስ ያልተቀነባበረ የሊቲየም ማዕድን ወደ ውጭ መላክ እንዲቆም የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ ማክበር አለብን” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።
ቀደም ሲል በኤመራልድ (መርግድ) ምርቷ ትታወቅ የነበረችው የሳንዳዋና ማዕድን ማውጫ፤ በዚምባብዌ ካሉ ቀዳሚ የሊቲየም ተስፋዎች አንዷ ስትሆን፤ አሁን ላይ የሀገሪቱን የሊቲየም ዘርፍ ለመደገፍ አቅጣጫዋን ቀይራለች ሲሉ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በዓለም ከቀዳሚዎቹ 10 የሊቲየም ክምችት ካላቸው ሀገራት አንዷ የሆነችው ዚምባብዌ፤ የሊቲየም ኢንዱስትሪዋን በከፍተኛ ፍጥነት እያሳደገች ትገኛለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X