የካሜሮን ፕሬዚዳንት የሀገሪቱን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እና የማዘጋጃ ቤት ምርጫ በድጋሚ አራዘሙ

ሰብስክራይብ

የካሜሮን ፕሬዚዳንት የሀገሪቱን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እና የማዘጋጃ ቤት ምርጫ በድጋሚ አራዘሙ

ፖል ቢያ የካቲት 3 ቀን ለወጣቶች በሚያደርጉት የተለመደ ንግግር በምርጫ የግዜ ሰሌዳው ላይ "ጥቂት ማስተካከያ" መደረጉን ጠቅሰዋል።

ለየካቲት 2026 ተይዞ የነበረው የካሜሮን መራጮች ጥሪ፤ "በአስገዳጅ ሁኔታዎች" ምክንያት ሕገ-መንግሥቱን በተከተለ መልኩ በድጋሚ ለሌላ ግዜ ተላልፏል ብለዋል።

የ93 ዓመቱ የሀገሪቱ መሪ አልፎ አልፎ በሚያደርጉት በዚህ ሕዝባዊ ንግግር የተነሱ ጉዳዮች፦

◻ የፓርላማ አባላት እና የማዘጋጃ ቤት ምክር ቤት አባላት የሥልጣን ዘመን መራዘም፣

◻ በመንግሥት ባለቤትነት ስር ባሉ ኩባንያዎች ውስጥ የአመራር ለውጥ ለማድረግ የሚደረጉ ዝግጅቶች፣

◻ በቅርቡ የሚዋቀረው አዲስ መንግሥት (ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚዋቀር ተገልጾ የነበረ ቢሆንም እስካሁን አልተፈጸመም)፣

◻ ወጣቶች ሥራ አጥነትን በጽናት እንዲጋፈጡ፣ ከወንጀል፣ ከአደንዛዥ ዕፅ፣ ከአልኮል ሱሰኝነት እና ከልክ ያለፈ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንዲርቁ የቀረበ ጥሪ፣

◻ በወጣት ሴቶች ላይ የሚፈጸመውን ትንኮሳ ለመከላከል የታወጁ እርምጃዎች፣

◻ ሙስናን ለመዋጋት እና በመንግሥት መዋቅር ላይ ለውጥ ለማምጣት የታደሱ ቃል ኪዳኖች።

የፖል ቢያን ከፊል ንግግር እንዲሁም ወጣት የካሜሮን ዜጎች ከመንግሥት የሚጠብቁትን ጉዳዮች በተመለከተ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ያደረጉትን ቃለ-መጠይቅ ለመመልከት ከላይ የተያያዘውን ተንቀሳቃሽ ምሥል ይከመልከቱ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0