የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለው የጉዞ እገዳ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ገቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተገለፀ
16:16 11.02.2026 (የተሻሻለ: 16:24 11.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለው የጉዞ እገዳ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ገቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተገለፀ
በጉዞ እገዳ ምክንያት ወደ አሜሪካ ከተሞች የሚጓዙ መንገደኞች ቁጥር መቀነሱን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ትናንት የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል።
“የአሜሪካ መንግሥት በየጊዜው ከጉዞ ጋር በተያያዘ የሚያወጣቸው እገዳዎች ወደ አሜሪካ ከተሞች በሚጓጓዙ መንገደኞቻችን ላይ ተጽዕኖ አሳድሮብናል” ብለዋል፡፡
ከየካቲት እስከ ግንቦት ባሉት አራት ወራት ውስጥ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ መንገደኞች ቁጥር እንደሚቀንስ ቢጠበቅም፤ የአሜሪካ መንግሥት በየጊዜው የሚጥላቸው የቪዛ እና ጉዞ ገደቦች ግን ችግሩን አባብሶታል ማለታቸውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ75 ሀገራት ዜጎች የፍልሰት ቪዛ መስጠት እንደምታቆም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባለፈው ጥር ወር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X