ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ለምግብ ዋስትና እና ለኑሮ ማሻሻያ የሚውል የ71.9 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ለምግብ ዋስትና እና ለኑሮ ማሻሻያ የሚውል የ71
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ለምግብ ዋስትና እና ለኑሮ ማሻሻያ የሚውል የ71 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.02.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ለምግብ ዋስትና እና ለኑሮ ማሻሻያ የሚውል የ71.9 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ

ከገንዘብ ድጋፍ ስምምነቱ 25.64 ሚሊዮኑ በዕርዳታ፤ ቀሪው 46.30 ሚሊዮን ዶላር በብድር መልክ የቀረበ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማዎች፦

የአርብቶ እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ ማኅበረሰቦች የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጋላጭነት እንዲቋቋሙ ማስቻል።

የአየር ንብረት ለውጥን ያገናዘቡ የፈጠራ ሥራዎችን፣ የዲጂታል የምክር አገልግሎቶችን እና የአየር ንብረት ፋይናንስ ተደራሽነትን ማቀናጀት።

የውሃ መሠረተ ልማቶች፣ የማኅበረሰብ መስኖ ልማት፣ የእንስሳት መገልገያ ተቋማት እና የታዳሽ ኃይል አማራጮችን ማስፋፋት።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሌክስ ሙቢሩ ተፈራርመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0