አየር ወለድ ትምህርት ቤት ልዩ ግዳጅ መፈፀም የሚችሉ ተዋጊ አየር ወለዶችን አሠልጥኖ አስመረቀ
19:13 10.02.2026 (የተሻሻለ: 19:24 10.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አየር ወለድ ትምህርት ቤት ልዩ ግዳጅ መፈፀም የሚችሉ ተዋጊ አየር ወለዶችን አሠልጥኖ አስመረቀ
ተመራቂዎቹ አዲስ ሠልጣኝ ሳይሆኑ ልዩ ግዳጅ የመፈፀም አቅማቸውን ለማጎልበት ተጨማሪ ሥልጠና የወሰዱ ነባር አየር ወለዶች እንደሆኑ፤ በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ገልፀዋል።
ሠልጠኝ አየር ወለዶቹ በየትኛውም የአየር ፀባይ፣ የመሬትና የውሃ ገፅታ በሌሊትም ሆነ በቀን በየትኛውም ቦታ በጠላት ወረዳ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ልዩ ግዳጅ የመፈፀም አቅማቸው የላቀ ደረጃ ላይ ደርሷል መባሉን መከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል፡፡
ተመራቂዎቹ ከተቋሙ የሚሰጣቸውን የትኛውንም ልዩ ግዳጅ ለመፈፀም ሁሌም ዝግጁ እንዲሆኑ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X