በአማራ ክልል አንድ ሕጻን የወተት ጥርስ አብቅሎ መወለዱ ተሰማ
18:17 10.02.2026 (የተሻሻለ: 18:24 10.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአማራ ክልል አንድ ሕጻን የወተት ጥርስ አብቅሎ መወለዱ ተሰማ
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያጋጠመው ይህ ክስተት በሆስፒታሉ ታሪክ የመጀመሪያ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሆኖም መሰል ክስተቶች የተለመዱ እና አዲስ ሕጻናት አልፎ አልፎ የወተት ጥርስ አብቅለው የመወለድ እድል እንዳላቸው በሆስፒታሉ አዋላጅ ነርስ የሆኑት መንግስቱ ኤባ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
የበቀለው የወተት ጥርስ በሕጻኑ ጤና ላይ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት ባይኖረውም ለቀጣይ የሕጻኑ ጥርስ አበቃቀል እንዲመች እንደሚወገድ ዘገባው አመላክቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X