በሞቃዲሾ አቅራቢያ የማረፊያ መስመሩን የሳተ የመንገደኞች አውሮፕላን ባሕር ውስጥ ገባ

ሰብስክራይብ

በሞቃዲሾ አቅራቢያ የማረፊያ መስመሩን የሳተ የመንገደኞች አውሮፕላን ባሕር ውስጥ ገባ

55 ሰዎችን ያሳፈረው የ "ስታርስኪ አቪዬሽን" አውሮፕላን በገጠመው የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ሞቃዲሾ ወደሚገኘው ኤደን አዴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በድንገት ለመመለስ መገደዱን የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

አውሮፕላኑ በድንገት ለማረፍ ሲሞክር ከማኮብከብያው ረድፍ በመውጣት በሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ውሃ ውስጥ ገብቷል፡፡

አብራሪው ለማረፍ ጥረት በሚያደርግበት ወቅት የአውሮፕላኑን ቁጥጥር ያጣ ሲሆን በውስጡ የነበሩ መንገደኞች በሙሉ በሰላም መውጣታቸውን እና በሰው ሕይወት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱን የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አህመድ መዓሊም ሀሰንን በመጥቀስ የሀገሪቱ የዜና ወኪል ዘግቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0