የበረሃ ሕዝቦችን የሚያስተሳስረው ዓለም አቀፍ የሰሃራ ባሕል ፌስቲቫል በቻድ እየተካሄደ ነው
16:09 10.02.2026 (የተሻሻለ: 16:14 10.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የበረሃ ሕዝቦችን የሚያስተሳስረው ዓለም አቀፍ የሰሃራ ባሕል ፌስቲቫል በቻድ እየተካሄደ ነው
ጥር 30 የተጀመረው ይህ ዝግጅት በርካታ ሳቢ ሁነቶች ወደሚስተናገዱበት ምዕራፍ ተሸጋግሯል።
ዋና ዋና ክስተቶች፦
የግመል ውድድር፦ የጽናት መለኪያ የሆነው የግመል ውድድር የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። ውድድሩ ከፉክክርነቱ ባለፈ ሕያው ቅርስ የሚከበርበት ሲሆን የቻድ፣ የኒጀር እና የቡርኪና ፋሶ ሚኒስትሮች በተገኙበት በሽልማት ሥነ-ሥርዓት ተጠናቋል።
ኪነ-ጥበብ፦ የሀገሪቱ ብሔራዊ ባሌ እና የተጋባዥ ሀገራት ልዑካን የሰሃራን ጥበባዊ ሀብት በሚያንጸባርቁ ትርዒቶች ባሕላዊ መንደሩን እያደመቁት ይገኛሉ።
ለባሕላዊ ውይይት ልዩ መድረክ የሆነው ፌስቲቫል እስከ የካቲት 6 የሚቀጥል ሲሆን በበረሃማ አካባቢዎች በሚኖሩ ማኅበረሰቦች መካከል ያለውን ትስስር እንደሚያጠናክር አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X