በቀጣይ ስድስት ወራት ከ1 ሺህ 200 በላይ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበቀጣይ ስድስት ወራት ከ1 ሺህ 200 በላይ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ተባለ
በቀጣይ ስድስት ወራት ከ1 ሺህ 200 በላይ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.02.2026
ሰብስክራይብ

በቀጣይ ስድስት ወራት ከ1 ሺህ 200 በላይ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ተባለ

በመላ ሀገሪቱ በሚገኙና ምንም አይነት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሌላቸው 626 ወረዳዎች አንድ አንድ ትምህርት ቤት እንደሚገነባ ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በዚህ ሀገራዊ ፕሮጀክት ተጠቃሚ የሚሆኑ ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች በየወረዳው በሚገነባው ትምህርት ቤት ተመሳሳይ ሌላ ትምህርት ቤት እንዲገነቡ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የትምህርት ቤቶቹ ዲዛይን ተሠርቶ መጠናቀቁን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ በቀጣይ ከክልሎች ጋር በመሆን ኮንትራክተሮችን በመለየት ግንባታው በፍጥነት እንደሚጀመር ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት ከ34 ሺህ በላይ ቅድመ አንደኛ ትምህር ቤቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ መገንባታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0