የአፋሮችን ባሕላዊ ሕግ ለማዋሃድ ያለመ ውይይት በሰመራ ተካሄደ
14:24 10.02.2026 (የተሻሻለ: 14:34 10.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፋሮችን ባሕላዊ ሕግ ለማዋሃድ ያለመ ውይይት በሰመራ ተካሄደ
በጂቡቲ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ናጂብ አብደላ መሐመድ ካሚል የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በውይይቱ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
የጋራ ውይይቱ በኢትዮጵያ፣ በጂቡቲ እና በኤርትራ የአፋር ማኅበረሰቦች ዘንድ ወጥ የሆነ የባሕላዊ ሕግ ማዕቀፍ ለመዘርጋት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የመድረኩ ትኩረት "አፋሬ ማድዓ" የተሰኘውን የአፋር ሕዝብ የጋራ ባሕላዊ የፍትሕ ስርዓት በአማራጭ የግጭት አፈታት መፍትሄነት ጥቅም ላይ ማዋል በሚቻልበት አግባብ ላይ መወያየት ነው፡፡
በሌላ በኩል፤ "አፋሬ ማድዓን" በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት በማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ ማስመዝገብም የውይይቱ አጀንዳ ነው።
"አፋሬ ማድዓ" ከፍትሕ ስርዓትነት ባለፈ ለዘመናት የዘለቀ የሰላም፣ የዕርቅ እና የማኅበራዊ ትስስር ዋልታ ሆኖ ያገለገለ ጥበብ እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia