ኢትዮጵያ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ሙሉ በሙሉ በበይነ-መረብ ልትሰጥ ነው
13:36 10.02.2026 (የተሻሻለ: 13:44 10.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ሙሉ በሙሉ በበይነ-መረብ ልትሰጥ ነው
ባለፉት ሁለት ዓመታት ሲሠራበት የነበረውን የወረቀት እና ዲጂታል ጥምር የፈተና አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል እንደሚያሸጋግር ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ለክልሎች አስፈላጊው ግብዓት እንዲሟላ በማድረግ፤ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች አስተማማኝ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲኖር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።
አክለውም የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች በቂ ኮምፒውተሮች፣ አስተማማኝ የኔትወርክ መሠረተ-ልማት እና ተለዋጭ የኃይል አቅርቦት እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል።
በተጨማሪም ተማሪዎች ከፈተናው በፊት በቂ የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና በማግኘት አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ባለፈው ዓመት 23.2 በመቶ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ብሔራዊ ፈተናን በበይነ መረብ መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X