በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የተገኘውን የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችትና ጥራት ለመለየት ጥናት ተጀመረ

© telegram sputnik_ethiopiaበአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የተገኘውን የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችትና ጥራት ለመለየት ጥናት ተጀመረ
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የተገኘውን የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችትና ጥራት ለመለየት ጥናት ተጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.02.2026
ሰብስክራይብ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የተገኘውን የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችትና ጥራት ለመለየት ጥናት ተጀመረ

በወረኢሉ እና ለገሂዳ ወረዳዎች መካከል ገንፍሎ ከወጣው የተፈጥሮ ነዳጅ ናሙና ተወስዶ የላቦራቶሪ ምርመራ እየተደረገለት እንደሚገኝ የዞኑ ማዕድን መምሪያ ኃላፊ አሕመድ አበባው ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።

በሳይንሳዊ ጥናቱ ላይ የማዕድን ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባና የወሎ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

“ጥናቱ በዋነኝነት የነዳጁን ክምችት መጠን፣ ጥራቱንና በዘርፉ ኢንቨስት ለማድረግ ያለውን ምቹነት ለማረጋገጥ ያለመ ነው” ብለዋል።

የምርምር ሥራው በተደጋጋሚና በተለያዩ የጂኦሎጂ ባለሙያዎች የሚከናወን በመሆኑ አጠቃላይ ውጤቱ የሚታወቅበትን ትክክለኛ ጊዜ አሁን መወሰን እንደማይቻል ኃላፊው አስረድተዋል።

የጥናቱ ውጤት እንደተጠናቀቀ ለፌዴራል ተቋማት ተልኮ በከፍተኛ ባለሙያዎች ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥበት አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0