ሮስቴክ የላቀ ብቃት ያለው 'ሳርማ' የተሰኘ አዲስ የሩሲያ የሚሳኤል ሥርዓትን ይፋ አደረገ
19:58 09.02.2026 (የተሻሻለ: 20:04 09.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሮስቴክ የላቀ ብቃት ያለው 'ሳርማ' የተሰኘ አዲስ የሩሲያ የሚሳኤል ሥርዓትን ይፋ አደረገ
በመንግሥት ባለቤትነት ስር የሚገኘው የሮስቴክ ኩባንያ ተቀጥላ ሮሶቦሮንኤክስፖርት፤ አዲሱን ባለ ብዙ አፈ-ሙዝ ሮኬት ማስወንጨፊያ ሥርዓት በሪያድ እየተካሄደ ባለው የ2026 ዓለም አቀፍ የመከላከያ ትርዒት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሳየቱን የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል።
ሥርዓቱ ሩሲያ በሮኬት መድፍ ውጊያ ካገኘችው ተሞክሮ በመነሳት የበለጸገ የ300 ሚሊ ሜትር ካሊበር መሣሪያ ነው።
'ሳርማ' ሙሉ በሙሉ በሩሲያ የኤሌክትሮኒክስ ክፍሎች የተገነባ፤ በኢላማ ትክክለኛነት እና በተኩስ ፍጥነት ላይ ከፍተኛ መሻሻል የታየበት የአዲሱ ትውልድ ቴክኖሎጂ ውጤት ነው።
መሣሪያው እስከ 120 ኪሎ ሜትር መምዘግዘግ የሚችል፣ ለውጊያ ዝግጁ ለመሆን ከ3 ደቂቃ በላይ የማይፈጅበት እንዲሁም በ18 ሰከንድ ውስጥ 6 ሮኬቶችን የመተኮስ አቅም አለው።
እነዚህ ብቃቶች በዓለም አቀፍ የባለ ብዙ አፈ-ሙዝ ሮኬት ማስወንጨፊያ ገበያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ የሚመደቡ መሆናቸውን የሮስቴክ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X