ኢትዮጵያ ከቡና የወጪ ንግድ አዲስ የገቢ ሪከርድ ለማስመዝገብ በምትችልበት አፋጻጸም ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ
19:29 09.02.2026 (የተሻሻለ: 19:34 09.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከቡና የወጪ ንግድ አዲስ የገቢ ሪከርድ ለማስመዝገብ በምትችልበት አፋጻጸም ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ
በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ለውጪ ገበያ ከቀረበው 200 መቶ ሺህ ቶን ቡና 1.345 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና የምትልክባቸው ሀገራት ቁጥር ወደ 84 ከፍ ማለቱንም የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻፊ ዑመር ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 600 ሺህ ቶን ቡና ለውጪ ገበያ በማቅረብ ሦስት ቢሊየን ዶላር በማግኘት ከፍተኛ አፈፃጸም ለማስመዝገብ እየሠራ መሆኑንም ኃላፊው ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት 469 ሺህ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ በመላክ 2.65 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ይታወቃል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X