በሞዛምቢክ በጎርፍ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር 724,131 ደረሰ

ሰብስክራይብ

በሞዛምቢክ በጎርፍ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር 724,131 ደረሰ

በሞዛምቢክ የጎርፍ አደጋ እስካሁን 170 ሺህ አባወራዎች የተጎዱ ሲሆን የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። ከ181,600 በላይ ቤቶች በጎርፍ ሲወሰዱ፤ በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

በተጨማሪም መንገዶች፣ ድልድዮች፣ የጤና ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች ላይ በደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ከ322 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተስተጓጉለዋል።

🫘 ለአደጋው ምላሽ ቀጣናዊ ትብብር ተጠናክሯል። ዛምቢያ 550 ቶን የምግብ እርዳታ (500 ቶን በቆሎ እና 50 ቶን ባቄላ) ያቀረበች ሲሆን ዚምባብዌ በበኩሏ ለሞዛምቢክ እና ለማላዊ የሚከፋፈል 2,000 ቶን እህል በጎርፍ የተጎዱ ማኅበረሰቦችን ለመርዳት ልካለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0