ኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች የናፍጣ ጄነሬተርን በድምፅ አልባ ስሪት የሚተካ አማራጭ ለገበያ አቀረቡ
18:36 09.02.2026 (የተሻሻለ: 18:44 09.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች የናፍጣ ጄነሬተርን በድምፅ አልባ ስሪት የሚተካ አማራጭ ለገበያ አቀረቡ
ፌድሆ ፓወር ሶሉሽን የተሰኘው ኩባንያ በፀሐይ ኃይልና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ድምፅ አልባ ጄነሬተሮችን ለገበያ እያቀረበ እንደሚገኝ የሀገር ውስጥ ሚድያ ዘግቧል።
የኩባንያው ተባባሪ መሥራች ፈድህሳ ሹማ፤ በተለይም ይኖርበት በነበረው ደምቢ ዶሎ ከተማ የኃይል መቆራረጥ በአነስተኛ የኤሌክትሮኒክስ ንግዱ ላይ የፈጠረበት ተጽዕኖ፤ ከዛም ገዝቶት የነበረው የነዳጅ ጀኔረተር መፈንዳቱ በሂደት ፈጠራው አሁን ለደርሰበት ደርጃ መነሻ እንደሆነ ተነግሯል።
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ሥራውን እያከናወነ የሚገኘው ኩባንያው፤ እስካሁን 35 ጀነሬተሮችን ለገበያ በማቅረብ 21 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘት መቻሉ ተገልጿል።
ኩባንያው አሁን ላይ ከ2 ኪሎ ዋት እስከ 500 ኪሎ ዋት አቅም ያላቸው ጀነሬተሮችን እያመረተ ሲሆን 58 በመቶ በላይ የሚሆኑት ክፍሎች በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X