ሱዳን ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ ኢጋድ አባልነቷ በይፋ ተመለሰች

ሰብስክራይብ

ሱዳን ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ ኢጋድ አባልነቷ በይፋ ተመለሰች

የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) "በአፍሪካ ቀንድ የጋራ ተግባራትን በመቅረጽ ረገድ የካርቱም ሚና እንዲመለስ የሚያደርግ እርምጃ" ሲል አወድሶታል።

"ሱዳን እንደ መስራች ሀገር፤ ወደ አባልነቷ መመለሷ የኢጋድን አንድነት የሚያጠናክር እና ቀጣናዊ የጋራ ቀዳሚ ጉዳዮችን የመፍታት አቅም የሚያሳድግ ነው" ሲሉ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ አስታውቀዋል።

ሱዳን፤ እ.ኤ.አ በጥር ወር 2024 በኡጋንዳ በተካሄደው የኢጋድ ስብሰባ የሀገሪቱ ግጭት አጀንዳ መደረጉን ተከትሎ "በውስጣዊ ጉዳዬ" ገብቷል በሚል አባልነቷን አግዳ እንደነበር ይታወሳል።

ከማህደር የተገኘው ተንቀሳቃሽ ምሥል ሱዳን ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበትን የኢጋድ ስብሰባ ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0