የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ፕሮጀክት ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ይዞ እየመጣ ነው ተባለ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ፕሮጀክት ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ይዞ እየመጣ ነው ተባለ

በአሁኑ ወቅት ፕሮጀክቱ በቴክኒክ ዝግጅት ምዕራፍ ላይ ቢሆንም የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ከወዲሁ ተስፋ ሰጪ ዕድሎች እያቀረበ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

‍ በአንድ ማመንጫ ጣቢያ ብቻ ከ800 በላይ የሚሆኑ ቋሚ፣ በሺዎች ለሚቆጠሩ ደግሞ ጊዜያዊ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ወጣቶችን ዋነኛ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በዘርፉ የሚሰማሩ ወጣቶች በሳይንስና በፈጠራ ያላቸውን አቅም በማሳደግ ዓለም አቀፍ ልምድ እንዲቀስሙ ዕድል ይሰጣል ተብሏል።

“የወደፊቷ ኢትዮጵያ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በከፍተኛ የኢንጂነሪንግ፣ የኳንተም ፊዚክስ እና የላቁ የምርምር ዘርፎች ሰልጥነው የሀገራቸውን ዕጣ ፈንታ በራሳቸው እውቀት የሚቀይሩበት አዲስ የሥልጣኔ ንጋት እየመጣ ነው” ሲል የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን በማኅበራዊ ትስስር ገፁ አጋርቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0