"የኤርትራ መንግሥት በአስቸኳይ ወታደሮቹን ከኢትዮጵያ ድንበሮች እንዲያስወጣ በይፋ እንጠይቃለን" – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"የኤርትራ መንግሥት በአስቸኳይ ወታደሮቹን ከኢትዮጵያ ድንበሮች እንዲያስወጣ በይፋ እንጠይቃለን" – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የኤርትራ መንግሥት በአስቸኳይ ወታደሮቹን ከኢትዮጵያ ድንበሮች እንዲያስወጣ በይፋ እንጠይቃለን – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.02.2026
ሰብስክራይብ

"የኤርትራ መንግሥት በአስቸኳይ ወታደሮቹን ከኢትዮጵያ ድንበሮች እንዲያስወጣ በይፋ እንጠይቃለን" – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፤ ለኤርትራው አቻቸው ጻፉት ተብሎ ኦንላይን ላይ እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ፣ ኤርትራ ከአማፂ ቡድኖች ጋር የምታደርገውን ትብብርንም በፍጥነት እንድታቆም ይጠይቃል፡፡

በቅርቡ የተካሄደውን ወታደራዊ ወረራ እና ከአማፂያን ጋር በጥምረት የተደረገው እንቅስቃሴ “ግልጽ ጥቃት” መሆኑንም ደብዳቤቤ ላይ ይነበባል፡፡

እንደ ደብዳቤው ከሆነ፣ ኢትዮጵያ የባሕር በር ተጠቃሚነትን እና የአሰብን ወደብን ጨምሮ ሉዓላዊነትን ባከበረ መንገድ በቅን ልቦና ለመነጋገር ዝግጁ ናት፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤውን በይፋ ባያወጣም፣ በምዕራባውያን ሚዲያ ላይ የተጠቀሱት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ነቢያት ጌታቸው፣ የደብዳቤውን ትክክለኛነት አረጋግጠዋል፡፡

ኤርትራ እ.አ.አ በ1993 መገንጠሏን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ ሆናለች። ከጥቂት ወራት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ኤርትራ እና ሕወሓት "ፅምዶ" ባሉት የጋራ ጥምረት ስር የጦርነት ሴራ እየሸረቡ ነው ሲል መክሰሱ ይታወሳል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0