ሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የፈፀሙትን ግፍ የኮነኑ ሀገራትን ስታመሰግን ዓለም አቀፉን ዝምታን ደሞ አውግዛለች
ሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የፈፀሙትን ግፍ የኮነኑ ሀገራትን ስታመሰግን ዓለም አቀፉን ዝምታን ደሞ አውግዛለች
"የሱዳን መንግሥት ለሱዳን ሰላምና አንድነት፣ ለሕዝቧ ደህንነት እና ለተቋሞቿ አንድነት ድጋፍ ለሚያደርጉ ወንድም እና ወዳጅ ሀገራት ያለውን አድናቆት ይገልጻል" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ይህ መግለጫ የወጣው በቅርቡ በሰሜን ኮርዶፋን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) የፈጸሙትን የድሮን ጥቃት ተከትሎ ነው። ጥቃቱ በዓለም የምግብ ፕሮግራም ኮንቮይ ላይ የተፈጸመ ሲሆን፣ አንዲት የዕርዳታ ሠራተኛ መገደሏንና ሌሎች መቁሰላቸውን፣ እንዲሁም በሌላ ጥቃት ደግሞ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ተመላክቷል።
መንግሥት የፈጥኖ ደራሹን ኃይሎች በጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ በሚፈጸም ሰብአዊ ወንጀል የከሰሰ ሲሆን፣ ጥቃቱን ለመፈጸም የተጠቀሙባቸው መሣሪያዎች ይፋዊ የዋና ተጠቃሚ የምስክር ወረቀት የሚጠይቁ ናቸው ብሏል። ይህም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዳርፉር ላይ የተጣለውን የመሣሪያ ማዕቀብ በመጣስ ከውጭ የሚገቡ መሆናቸውን ያሳያል ሲል ገልጿል።
ይህ ጥሰት የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተዓማኒነትን የሚያሳጣ መሆኑን ያስጠነቀቀው መግለጫው፣ ካርቱም “ሞግዚትነትን አትቀበልም” በማለት ዝምታን ከመረጡ ወይም ተባባሪ ከሆኑ ወገኖች ጋር ባላት የአጋርነት አቋም እንደማትቀጥል አውጇል።
ሚኒስቴሩ አፅንዖት ሰጥቶ እንደገለጸው፣ ጦርነቱ ማብቃት ያለበት የጥቃት መንስኤዎችን በመፍታት እና ጥፋተኞችን ተጠያቂ በማድረግ እንጂ ከውጭ በሚጫኑ መፍትሄዎች አይደለም።
ጥቃቱን ያወገዙትን የሱዳን አጋሮች ለማየት ቪዲዮውን ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X