የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በማላዊ ለሚገኙ አማኞቿ 46 ቶን ሰብአዊ እርዳታ ላከች
20:05 08.02.2026 (የተሻሻለ: 20:14 08.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በማላዊ ለሚገኙ አማኞቿ 46 ቶን ሰብአዊ እርዳታ ላከች
በዋነኝነት የበቆሎ ዱቄት፣ የአኩሪ አተር ዱቄት እና የምግብ ዘይትን ያካተተው ይህ እርዳታ፤ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአፍሪካ ፓትርያርክ መምሪያ አማካኝነት የተሰበሰበ ነው።
እስካሁን ወደ 975 የሚጠጉ የማላዊ ቤተሰቦች እርዳታውን አግኝተዋል።
በአጠቃላይ 2,700 የኦርቶዶክስ አባወራዎች ከእነዚህ የምግብ ጥቅሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እነዚህን 46 ቶን ምርቶች ለመግዛት የሚያስፈልገው ገንዘብ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የበጎ አድራጎት ተቋም አማካኝነት የተሰበሰበ ነው።
ምስሉ በቺክዋዋ ቀጠና የሚገኘው ደብር አማኞች ለተደረገላቸው እርዳታ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ሲያመሰግኑ ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/3
© telegram sputnik_ethiopia

2/3
© telegram sputnik_ethiopia

3/3
© telegram sputnik_ethiopia
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
3/3
© telegram sputnik_ethiopia