ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 27,773 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝሮባታል – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 27,773 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝሮባታል – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 27,773 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝሮባታል – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.02.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 27,773 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝሮባታል – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

አገሪቱ ከተሰነዘሩባት ጥቃቶች 99 በመቶ (27,505) የሚሆኑን በተሳካ ሁኔታ ማምከኗን አስተዳደሩ በግማሽ ዓመት ሪፖርቱ ላይ ገልጿል፡፡

ወደ ቢገቡ የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ 196 የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ማድረግ መቻሉንም ገልጿል፡፡

አስተዳደሩ ከቀረቡለት 253 የፎረንሲክ የምርመራ ጥያቄዎች መካከል ለ245ቱ ለ96.8 በመቶ ምላሽ ሰጥቷል።

በተጨማሪም ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ሕሊና ግንባታ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ የዋለ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ለ14 ተቋማት የሳይበር ደህንነት መፍትሔዎችና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠቱንም አስተዳደሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አስነብቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0