እስራኤል ወታደሮቿን ወደ ሶማሊላንድ ከላከች እንዋጋቸዋለን - ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ
18:16 08.02.2026 (የተሻሻለ: 18:24 08.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
እስራኤል ወታደሮቿን ወደ ሶማሊላንድ ከላከች እንዋጋቸዋለን - ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ
የሱማሊያው ፕሬዝዳንት፣ እስራኤል ራሷን ከሶማሊያ በነጠለችው ሶማሊላንድ ውስጥ ወታደሮቿን ልታሰፍር ትችላለች ተብሎ በአልጀዚራ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፦ "ባለን አቅም ሁሉ እንዋጋለን ... ራሳችንን እንከላከላለን ... ይህንንም እንቃወማለን፤ በፍጹምም አንፈቅድም" ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በሶማሊላንድ ውስጥ የሚገኝ ምንም ዓይነት የእስራኤል ጦር የሌለ ሲሆን፣ የሶማሊያ ባለሥልጣናትም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይመጣሉ ብለው እንደማይጠብቁ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት መሀሙድ ባለፈው ታህሳስ የደኅንነት መረጃዎችን ጠቅሰው እንደተናገሩት፣ እስራኤል ሶማሊላንድን በሀገርነት እውቅና ለመስጠት ካስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ በኤደን ባህረ ሰላጤ ዳርቻ ላይ የጦር ሰፈር መመስረት ነው።
እስራኤል ከሶማሊያ የተገነጠለችውን ሶማሊላንድን የሀገርነት እውቅና የሰጠች በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ ሀገር ነች። ሆኖም በርካታ ሀገራት እና ድርጅቶች ይህ እውቅና የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው በሚል በጽኑ አውግዘውታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X