የሩሲያ የሳይንስ ዘርፍ የቴክኖሎጂ መሪነትን ለማሳካት ቁልፍ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ
17:52 08.02.2026 (የተሻሻለ: 17:54 08.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ የሳይንስ ዘርፍ የቴክኖሎጂ መሪነትን ለማሳካት ቁልፍ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ
የሩሲያ የሳይንስ ቀንን አስመልክቶ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ቼርኒሼንኮ እንደተናገሩት፣ ሀገሪቱ በሳይንሱ መስክ ይበልጥ እየጠነከረችና በራሷ እየተማመነች የመጣች ሲሆን፣ ይህም ለሀገሪቱ ዓለም አቀፋዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
ከመግለጫቸው የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 የወጣት ተመራማሪዎች ቁጥር እና ለሳይንስ ዘርፍ የሚመደበው የገንዘብ ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
🟠 ሩሲያ በምርምር እና ልማት አቅም (ምጣኔ) በዓለም ላይ ካሉ ቀዳሚ አስር ሀገራት ተርታ ተሰልፋለች።
🟠 በዚህ ዓመት "ወጣቶች እና ሕፃናት" በተሰኘው ብሔራዊ ፕሮጀክት አማካኝነት ከ1,100 በላይ የወጣቶች የምርምር ላቦራቶሪዎች ይቋቋማሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X