ካርቱም የሱዳን ግጭት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀ የአበባ ፌስቲቫል ዳግም "አበበች"

ሰብስክራይብ

ካርቱም የሱዳን ግጭት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀ የአበባ ፌስቲቫል ዳግም "አበበች"

​ የሱዳን መዲና ካርቱም፣ ከሦስት ዓመታት በፊት ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ትልቅ የሕዝባዊ አበባ ፌስቲቫል እያስተናገደች ትገኛለች። አዘጋጆቹ፣ ዝግጅቱን ለከተማዋ ማገገም እንደ "የተስፋ መልዕክት" እንደሚቆጠር ገልጸውታል።

​ "ሽትላ" የተሰኘው የአበባ ኤግዚቢሽን በዛሬው ዕለት በማሪና ፓርክ የተከፈተ ሲሆን እስከ የካቲት 7 ቀን ድረስ ይቆያል። ከመላው ሱዳን የተውጣጡ ከ150 በላይ ኩባንያዎች ተክሎችን፣ ችግኞችን፣ የአትክልት ስፍራ ዲዛይኖችን እና ብርቅዬ አበቦችን ይዘው ቀርበዋል።

​ፌስቲቫሉ ወደ መደበኛ ሕይወት ለመመለስ እና ለመታደስ እንደ ተምሳሌታዊ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ 'የካርቱም ዳግም ትንሳኤ መንፈስ' ብለው የሚጠሩትን ስሜት የሚያንጸባርቅ ነው።

ምስሎቹ ከማኅበራዊ የትስስር ገፆች የተገኘ ናቸው

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0