ደቡብ አፍሪካ ከ27 ዓመታት በኋላ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወታደሮቿን ልታስወጣ ነው፦ የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት

ሰብስክራይብ

ደቡብ አፍሪካ ከ27 ዓመታት በኋላ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወታደሮቿን ልታስወጣ ነው፦ የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት

​ ውሳኔው የደቡብ አፍሪካን የመከላከያ ሀብት ስልታዊ በሆነ መልኩ እንደገና የማደራጀት አካል መሆኑን የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል።

​እንደ መግለጫው ከሆነ፤ ከ700 በላይ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮችን ከኮንጎ የማስወጣቱ ሂደት እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2026 መጨረሻ ድረስ ይጠናቀቃል።

​ እ.ኤ.አ. ከ1999 የመስከረም ወር ጀምሮ በተመድ ተልዕኮ ውስጥ ስትሳተፍ የቆየችው ደቡብ አፍሪካ፤ ከኮንጎ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንደምታስቀጥልና ሌሎች ባለብዙ ወገን የሰላም ጥረቶችን መደገፏን እንደምትቀጥል አስታውቃለች።

​በጎርጎሮሳዊያኑ 2025፣ ደቡብ አፍሪካ በምስራቅ ኮንጎ የነበረው የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በይፋ ማብቃቱን ተከትሎ ወታደሮቿን ከሀገሪቱ ማስወጣቷ ይታወሳል።

ቪዲዮው ወታደሮቹ  በጎርጎሮሳዉያኑ ሰኔ 2025 ወደ አገራቸው ሲመለሱ ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0