የጎርጎሮሳውያኑ 1949 የኤኑጉ ማዕድን አውጪዎች ጭፍጨፋ - የናይጄሪያ የፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል ምልክት ስለሆነው ክስተት የምናውቀው እውነታ

ሰብስክራይብ

የጎርጎሮሳውያኑ 1949 የኤኑጉ ማዕድን አውጪዎች ጭፍጨፋ - የናይጄሪያ የፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል ምልክት ስለሆነው ክስተት የምናውቀው እውነታ

▪ እ.ኤ.አ ህዳር 18 ቀን 1949 በደቡብ ምስራቅ ናይጄሪያ በሚገኘው "ኢቫ ቫሊ" የድንጋይ ከሰል ማዕድን ማውጫ፣ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ፖሊሶች የሥራ ማቆም አድማ እያደረጉ በነበሩ ያልታጠቁ ማዕድን አውጪዎች ላይ ተኩስ ከፈቱ። ይህ ክስተት በናይጄሪያ የቅኝ ግዛት ዘመን ታሪክ ውስጥ እጅግ አሳዛኝ እና ጉልህ ከሆኑ ክስተቶች አንዱ ሆኖ ይቆጠራል።

​▪ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነበር፤ 21 ማዕድን አውጪዎች ሲገደሉ 51 ደግሞ ቆስለዋል።

​▪የሰራተኞቹ የተቃውሞ ምክንያቶች፦

• ​አስቸጋሪ እና አደገኛ የሥራ ሁኔታዎችን፣

• ጅግ ዝቅተኛ ደመወዝ እና ግልጽ የሆነ የዘር መድልዎ በመቃወም (አውሮፓውያን ሰራተኞች እጅግ የላቀ ክፍያ ይከፈላቸው ነበር)፣

• ​ያልተከፈለ ደመወዝ እና ያለአግባብ ከሥራ መባረርን በመቃወም ነበር።

▪ በአፍሪካ የማዕድን ሰራተኞች ማህበር ይደገፍ የነበረው አድማ መጀመሪያ ላይ ሰላማዊ የነበረ ቢሆንም፣ የሥራ አመራሩ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ከሥራ ካሰናበተ በኋላ ሁኔታው ተባባሰ።

​▪ ተኩስ በተከፈተባቸው ዕለት፣ ማዕድን አውጪዎቹ የማዕድን መቆፈሪያ መሣሪያዎችና ፈንጂዎች እንዳይወሰዱ ለመከላከል በሰላማዊ መንገድ ቦታውን ይዘው ነበር።

​▪ የእንግሊዝ ፖሊስ የበላይ ተቆጣጣሪ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት፣ ከእንግሊዝ እና ከናይጄሪያ የተውጣጡ የደህንነት ኃይሎች "አደጋ ተጋርጦብናል" በሚል ሰበብ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ተኩስ ከፈቱ።

▪ በወቅቱ ምርመራዎች ተካሂደው የነበረ ቢሆንም፣ የቅኝ ግዛት ባለሥልጣናትን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርጉ ነበሩ።

​ የፍትሕ መስፈን፦ ጥር 29፣ 2018፣ የኤኑጉ ግዛት ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእንግሊዝ መንግሥት ለተገደሉት ማዕድን አውጪዎች ቤተሰቦች 572 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍል ወሰነ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0